አሸንጎዳ ፐሮጀክት

የፈረንሳይ የልማት ድርጅት (AFD) ከ1985ዓ.ም ጀምሮ ፈቃድ አግኝቶ በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀስ ያለ የልማት ድርጅት ነው። ከ 1999 ዓ.ም ጀምሮ በታለመላቸው አካባቢዎች በሙሉ እንቅስቃሴ እያደረገ መጥቷል፣ ለአገሪቱ ልማት ለተነደፈው እስትራቴጂ በአጋርነት ይሰራል።

የበለጠ ለማወቅ

የወቅቱ እድገት
ውሃ ፕሮጀክት

የፈረንሳይ የልማት ድርጅት (AFD) በአሁኑ ጊዜ በመስክ የውሃ ልማትና የንጽህና፣ የመብራት ሓይል፣ የግል አምራቾች፣ የከተማና የተራንስፖርት መሰረተልማት ክፍሎች ላይ ፋይናንስ እያደረገ ይገኛል።

ፐሮጀክት

ወሳኝ ፐሮጀክቶች

በፈረንሳይ ልማት ድርጅትና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የምርምር አጋርነት በድጋሚ ማጠናከር

24/11/2016

የፈረንሳይ ልማት ድርጅትና ኢትዮጵያ በፐበሊክ ፖሊሲ ምርምር ስራ ላይ ያላቸውን ትብብር እንደገና ለማረጋገጥ የ 200 000 ዮሮ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

 

የፈረንሳይ ልማት ድርጅትና ( AFD ) የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት (EDRI) ታሕሳስ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. የፈረሙት  ሰተራቴጂያዊና የፋይናነስ የአጋርነት ስምምነት የምርምርና ድጋፍ ፕሮገራምን ተግባራዊ በማድረግ በአገሪቱ የኢንድስተሪና የመዋቅራዊ ሽግግርን ፖለቲካ ለማጎልበት የታለመ ነው።

 

የዚህ ፕሮገራም ሁለተኛ ዙር አዳዲስ ተግባራትን ጨምሮ አጋርነትን በማጠናከር መልኩ ታሕሳስ 15 ቀን 2009 ዓ.ም. ስራ እንዲጀምር ተደርጓል። ቅድሚያ የተሰጠው ተግባርም በ ኢትዮጵያ የልማት ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎችና በፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲ እና የምርምር ማዕከል (Toulouse School of Economics and the French statistical agency, INSEE) መካከል ትብብር ማደረግ ነው። ቁልፍ ጉዳዮች ሆነው የተመረጡትም እንደ ቆዳና ሌጦ ጥራት፣ በከፍተኛ ጥራት ደረጃ የቆዳ ኢነደስትሪን ለገበያ ማቅረብ እና የኢንደስተሪ ፓረኮች በቅጥር(በስራ ፈጠራ ) ላይ የሚኖራቸውን ተጽእኖ የሚያጠቃልል ይሆናል። እንዲሁም የፈረንሳይ ልማት ድርጅት ( AFD ) የአዲስ አበባ ኤጀንሲ እእአ በ2017ዓ.ም. 20ኛ ዓመት ክበረ በአሉን ሲያደረግ የ ፐብሊክ ፖሊሲን የጋራ ጉዳዮች ለመወያት የሚያስችል ፐሮገራም እንዲዘጋጅ ይደረጋል።

 

የትብብር ስምምነቱ የተደረገው በሚኒስትር መኣረግ አዲስ በተሾሙት የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሪክተር በሆኑት አቶ መኮንን ማንያዘዋል እና በአዲስ አበባ የፈረንሳይ ልማት ሪጂናል ዳይሪክተር Mr. Ignace Monkam-Daverat መካከል ነው። ይህ ትብብር የፈረንሳይ ልማት ድርጅትን ( AFD ) ፈይናንስ ነክ የሆኑና ያለሆኑትን የልማት ዘርፍ መሳሪያዎቹን አቅም ለመጠቀም እንዲችል በድጋሚ የሚያረጋግጥ ሲሆን በኢትዮጵያ የፐብሊክ ፖሊሲ ክርክር ውስጥም የፈረንሳይን አቋም የሚያጠናክር ይሆናል።    

 ጣሊያን ፣ ፈረንሳይ እና የአውሮፓ መዋእለ ነዋይ ባንክ በጋራ በመሆን የከተማ ውሃ፣ ንጽህና እና የጤና አጠባበቅን በተመለከተ የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራረ

04/10/2016

የጣሊያን ኤጀንሲ ለልማትና ትብብር (AICS) የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) ፣ የአውሮፓ የመዋእለ ነዋይ ባነክ (EIB) እና በጋራ በመሆን የብዙ ፋይናንሰሮች የጥምር ተነሳሽነትን ማእቀፍ በማድረግ የከተማ ውሃ፣ ንጽህና እና የጤና አጠባበቅን በተመለከተ የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርመዋል።

ኢትዮጵያ አነስተኛና መካከለኛ ለሆኑ ከተሞች የንጹህ ወሃና የንጽህና አጠባበቅ ተደራሽነት ፕሮግራም መነሻ ያደረገ በአማካኝ በአገር አቀፍ ደረጃ 40 ከተሞች ወሳኝ ከሆነው የመጠጥ ውሃ፣ የፍሳሽና የጤና አጠባበቅ መሰረተለማት መዋእለ ነዋይ ተጠቃሚ ሆነዋል። በግምባር ቀደምትነት የሚገኙ የአውሮፓ የልማት ፋይናንስ ድርጅቶች 81.4 ሚሊዪን ዮሮ ያገዙ ሲሆን ፕሮገራሙም በአገሪቱ ውስጥ   የንጹህ   ውሃና የንጽህና አጠባበቅ አገልግሎትን ለማሻሻል የታለመ ነው።

በዚህ ማእቀፍ ውስጥ የጣሊያን ኤጀንሲ ለልማትና ትብብር (AICS) ፣ እና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) እና የአውሮፓ የመዋእለ ነዋይ ባነክ (EIB) የጋራ ፋይናንስ ተነሳሽነት  በማሳየት የመግባቢያ ሰነዱን ፈረመዋል።

ፕሮገራሙ የሚተገበረው በሶስቱ የፋይናንስ ደጋፊዎች አማካኝነት የውሃ፣ መስኖና አሌክትሪክ ሚኒሰቴር አካል በሆነው  የውሃ ሃብት ልማት ፈንድ (WRDF) ይሆናል። የተመቻቸው የገንዘብ መጠን 40ሚሊን ዮሮ በአነስተኛ ወለድ እና 1.9 ሚሊን ዮሮ በስጦታ ከአውሮፓ የመዋእለነዋይ ባነክ (EIB) የ20 ሚሊዮን ዮሮ የአነስተኛ ወለድ እና የ 1 ሚሊዮን ዮሮ ስጦታ ከ ፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) እና 15 ሚሊዮን ዮሮ የአነስተኛ ወለድ ብድርና 3.5 ሚሊዮን ዮሮ ስጦታ ከጣሊያን ኤጀንሲ ለልማትና ትብብር (AICS)    የተገኘ ነው። ከለይ የተጠቀሱት በአነስተኛ ወለድ የተገኙት ብድሮች ለመሰረተልማቱ ወጪ የሚውሉ ሲሆን በስጦታ የተገኘው ገንዘብ ደግሞ ውሃ ሃብት ልማት ፈንድ፣ ለክልል ውሃ ቢሮና ለከተሞች የውሃ አገልግሎት ቢሮዎች አቅም ግንባታ የሚውል ይሆናል።

ይኽ የመግባቢያ ሰነድ   በፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖበለክ ኢትዮጵያና በአፍሪካ ህብረት የፈረንሳይ አምባሳደር የሆኑት የተከበሩ Mr. Frédéric Bontems በተገኙበት Mr Christophe Litt   EIB ተወካይ፣   Mr Ignace Monkam-Daverat የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ አዲስ ዳይሪክተር እና የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉት የጣሊያን ኤጀንሲ ለልማትና ትብብር  ዳይሪክተር በሆኑት በ Ms. Laura Frigenti መካከል ተፈርሟል

በዚህ የመግባቢያ ሰነድ አማካኝነት ሶስቱም የእድገት ተባባሪዎች ሁሉንም የፕሮገራም እንቅስቃሴዎች  የተጣጣመ እንዲሁም የበለጠ  አሰሪና አጥጋቢ ለማድረግ ተመሳሳይ የሆነ መመሪያና ፕሮሲጀር በመከተል ፕሮገራሙን ለማስፈጸም ተስማምተዋል።አዲስ የአስተዳደር ቡድን (New managing team) በፈረንሳይ ልማት ድርጅት (AFD)፣

01/09/2016

የፈረንሳይ ልማት ድርጅት አዲሱን የአስተዳደር ቡድን በጋለ ስሜት የተቀበለ ሲሆን Mr. Ignace Monkam-Daverat የቀድሞው ድርጅቱ ዳይሪከተር የነበሩትን  Mr. Christian Yoka ተክተዋቸዋል እንዲሁም Mr. Shayan Kassim የፕሮጀክት ማኔጀር የነበሩትን  Ms. Anne Chapalain ተክተዋቸዋል። ሁለቱ የድርጅቱ አመራሮች በነሃሴ አጋማሽ ላይ ስራ ጀምረዋል።

 

New Team - Ignace Monkam - Daverat

በእርሻ ምህንድስና ባለሞያነትና  በፋይናንስ ዘርፍ የተደገፈ እውቀት ያላቸው  Mr. Ignace Monkam-Daverat በፈረንሳይ ፓሪስ በሚገኘው ዋናው የፈረንሳይ ልማት ድርጅት እና በአፍሪካ ውስጥ በሴኔጋል፣ኬፕቨርዲ፣ታንዛኒያ ፣ዩጋንዳ እና ወደ አዲስ አበባ አስከተዛወሩበት አስካለፈው ነሃሴ አጋማሽ ድረስ በጂቡቲ፣ የመንና ሱማሊላነድን ጨምሮ  የሪጂናል ዳይሪክተር  የነበሩ ሲሆን በሰሩባቸው የፕሮጀክት ኦፊሰርነት፣ በፕሮጀክት ማኔጀርነትና ዳይሪክተርነት ኃላፊነት ወደ20 ዓመት የሚጠጋ የአገልግሎት ያላቸው ናቸው።

 

  

New Team - Shayan Kassim

የምህንድስና ባለሞያ የሆኑት Mr. Shayan Kassim የፈረንሳይ የልማት ድርጅትን እአአ በ2012 የውስጥ ኦዲት ቡድን አባል ሆነው ከመቀላቀላቸው በፊት ለአምስት ዓመታት ያህል በፈረንሳይ የባነክ ቡድን ውስጥ (Société Générale CIB) በዋነኝነት የብድር  አቅርቦት ላይ ሲሰሩ ቆይተዋል። በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ የፈረንሳይ ልማት ድርጅት ውስጥ የከተማ ልማት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ የፕሮጀክት ማኔጀር በመሆን የተመደቡ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የሪጅናል ዳይሬክተሩን ቦታ ተክተው ይሰራሉ። 
 
1 
2  3  4  5   ... 
 
 
Archives

Test